ለማርያም ለማርያም

ለማርያም ለማርያም
እንዘምራለን ለዘላለም
የተዘጋች ደጅ ........................ ለዘላለም
ህዝቅኤል ብሏል ........................ ለዘላለም
ንጽህት ናት በእውነት ........................ ለዘላለም
በፍጹም ድንግል ........................ ለዘላለም
አብነት አድርገን ........................ ለዘላለም
እኛም እርሱን ........................ ለዘላለም
በፍጹም ፍቅር እንዘምራለን
አዝ.....
የዋሂት ርግብ ........................ ለዘላለም
ሰላም አብሳሪ ........................ ለዘላለም
ጨለማ ህይወቴን ........................ ለዘላለም
ብርሃንን አብሪ ........................ ለዘላለም
እማጸንሻለሁ ........................ ለዘላለም
ድንግል ለነብሴ ........................ ለዘላለም
አደራ ድንግል አንቺ ነሽ ዋሴ
አዝ......
እጅግ የበዛ ነው ........................ ለዘላለም
ያለኝ ፍቅር ........................ ለዘላለም
አይወሰንም ........................ ለዘላለም
አይነገርም ........................ ለዘላለም
በርሷ ደስ ይለኛል ........................ለዘላለም
ሀሴት አደርጋለሁ ........................ ለዘላለም
ስሟን እየጠራሁ እዘምራለሁ
አዝ......
ንዒ ንዒ ስላት ........................ ለዘላለም
ቀንና ሌሊት ........................ ለዘላለም
አትለየኝም ........................ ለዘላለም
ለኔስ ቅርቤ ናት ........................ ለዘላለም
እጹብ እጹብ ብለው ........................ ለዘላለም
አመሰገኗት ........................ ለዘላለም
ክብሯን ሊገልጡ ቢያጥራቸው ቃላት
← መዝሙር