ለማርያም

ለማርያም
እንዘምራለን ለዘለዓለም
የተዘጋች ደጅ ለዘለዓለም
ሕዝቅኤል ብሏል
ንጽሕት ናት በእውነት
በፍጹም ድንግል
አብነት አድርገን
እኛም እርሷን ለዘላለም
በፍጹም ፍቅር አንዘምራለን
የዋህት ርግብ ለዘለዓለም
ሰላም አብሳሪ ለዘለዓለም
ጨለማ ሕይወቴ ለዘለዓለም
በርሃንን አብሪ ለዘለዓለም
እማጸንሻለሁ ለዘለዓለም
ድንግል ለነፍሴ ለዘለዓለም
አደራ ቅድስት አንቺ ነሽ ዋሴ
እጅግ የበዛ ነው ለዘለዓለም
ያለኝ ፍቀር ለዘለዓለም
አይወሰንም ለዘለዓለም
አይነገርም ለዘለዓለም
በእርሷ ደስ ይለኛል ለዘለዓለም
ሐሴት አደርጋለሁ ለዘለዓለም
ሰሟን እየጠራሁ እዘምራለሁ
ነይ ነይ ስላት ለዘለዓለም
ቀንና ሌሊት ለዘለዓለም
አትለየኝም ለዘለዓለም
ለእኔስ ቅርቤናት
እጹብ እጹብ ብለው ለዘለዓለም
እመሰገኗት ለዘለዓለም
ክብሯን ሊገልጹት ቢያጥራቸው ቃላት
← መዝሙር