ለምኚ ድንግል

ለምኚ ድንግል ለምኚ
ለኃጥአን አይደለም ለጻድቃን
ለምኚ ታላቅ ስጦታዬ
ለምኚ አዛኝ ሩኅሩኅ ነሽ
ለምኚ የጌታዬ እናት
ለምኚ ጸጋን የተሞላሽ
ለምኚ የአምላክ ማደሪያ
ለምኚ ለምነሽ አስምሪን
ለምኚ አማናዊት ጽዮን
ለምኚ ከእኛ አትለይኝ
አዝ--------------
ለምኚ ሐዘንሽ አዘኜ
ለምኚ ለእኔ ይሁን ድንግል
ለምኚ የተንከራተትሽው
ለምኚ በሀገረ እስራኤል
ለምኚ ትእግሥትሽን ሳየው
ለምኚ ልቤ ይመሰጣል
ለምኚ የሐዘን እንባ ጎርፍ
ለምኚ ዓይኔን ይሞላዋል
አዝ------------------
ለምኚ በቀራንዮ አምባ
ለምኚ በዚያ የፍቅር ቦታ
ለምኚ በእግረ መስቀሉ ሥር
ለምኚ ከክርስቶስ ጌታ
ለምኚ ለእኛ ተሰጥተሻል
ለምኚ እናት እንድትሆኝን
ለምኚ ልጆችሽ ነንና
ለምኚ ምልጃሽ አይለየን
አዝ----------
ለምኚ አንደበቴን ጌታ
ለምኚ በምስጋና ምላው
ለምኚ ደስ ይበልሽ ብዬ
ለምኚ እኔም ላመስግናት
ለምኚ አንደበቴን ጌታ
ለምኚ በምስጋና ምላው
ለምኚ ደስ ይበልሽ ብዬ
ለምኚ እኔም ላመስግናት
አዝ----------
← መዝሙር