ለምትቀር ዓለም

ለምትቀር ዓለም
ለምትቀር ዓለም መታከት መድከም
በዓለም በረሀ ወድቀን እዳንጠፋ
መጽናት ገባልናል በፍቅር በደስታ
እምነት ተስፋ ፍቅር እነዚህን ይዘን
ድል ማድረግ አለብን የምትቀር ዓለምን
አዝ ---
በሥጋዊ ምኞት በዓለም ተጠምደን
የአምላካቸንን ትእዛዙን ጥሰን
ከፈጣሪያችን ፊት ከቤቱ እንዳንጠፋ
ወላዲተ አምላክ አንቺ ሁኝን ተስፋ
አዝ ---
በሲኦል በረሀ እንዳንቀር ወድቀን
ልንቆም ይገባናል በእምነት ተደግፈን
ጌታችን ሲመጣ በግራ ከመቆም
ካሁኑ እንዘጋጅ ነገ የእኛ አይደለም
አዝ ---
እንደ ሰማእታት ዓለምን በመናቅ
ጽድቅን እየሠራን ከክፋት በመራቅ
እንዘን አናልቅስ ስለበደላችን
በቀኙ እንዲያቆመን ቸሩ ፈጣሪያችን
አዝ ---
← መዝሙር