ለውለታህማ
✦
ለውለታህማ ጌታ ምን እንከፍልሃለን
ለማይነገር ስጦታህ ተመስገን እንልሃለን፪
ማቃችንን ቀይረህ አዲስ ላለበስከን
ቁስላችንን አጥበህ ዘይት ለቀባኸን
ጠላት ሲያዋርደን አንተ ላከበርከን
ለዚህ ሁሉ ውለታህ ምን እንከፍልሃለን
እኛ በበደልን ትእዛዝህን ጥሰን
አንተ በመስቀል ላይ ደምህ ፈሰሰልን
ፍቅርህን ስናስብ እጅግ ይድነቀናል
ለዚህ ሁሌ ውለታህ ምን ይከፈልሃል
የእኛ ፍቅር ስቦህ ከሰማይ ወርደህ
ደካማ ሥጋችንን ተዋርደህ አክብረህ
እግራችንን አጥብህ ፍቅር ላስተማርከን
ውለታህ ከብዶናል ምን እንከፍልሃለን፪
ባሮች እንዳልነበርን ልጆች አደረከን
መቼም ከማያልቀው በረከት አደልከን
ዘለአለማዊ ሕይወት ለሰጠኸን
ምስጋናችን ይድረስኽጸጋህ አይለየን
ለማይነገር ስጦታህ ተመስገን እንልሃለን፪
ማቃችንን ቀይረህ አዲስ ላለበስከን
ቁስላችንን አጥበህ ዘይት ለቀባኸን
ጠላት ሲያዋርደን አንተ ላከበርከን
ለዚህ ሁሉ ውለታህ ምን እንከፍልሃለን
እኛ በበደልን ትእዛዝህን ጥሰን
አንተ በመስቀል ላይ ደምህ ፈሰሰልን
ፍቅርህን ስናስብ እጅግ ይድነቀናል
ለዚህ ሁሌ ውለታህ ምን ይከፈልሃል
የእኛ ፍቅር ስቦህ ከሰማይ ወርደህ
ደካማ ሥጋችንን ተዋርደህ አክብረህ
እግራችንን አጥብህ ፍቅር ላስተማርከን
ውለታህ ከብዶናል ምን እንከፍልሃለን፪
ባሮች እንዳልነበርን ልጆች አደረከን
መቼም ከማያልቀው በረከት አደልከን
ዘለአለማዊ ሕይወት ለሰጠኸን
ምስጋናችን ይድረስኽጸጋህ አይለየን
✦