ልቤ በእግዚአብሔር ጸና

ልቤ በእግዚአብሔር ጸና
አፌን አላቀኩኝ ለስሙ ምስጋና
አዝ--------------------//
በጠላቶቼ ላይ አፌ ተከፈተ
ማዳኑን አይቼ ልቤ ተደሰተ
እንደ እግዚአብሔር ያለ ረዳት ማን አለ
ደካማ ባርያውን ስለተቀበለ
አዝ--------------------//
ጠግበው የነበሩ እንጀራን ተራቡ
ተርበው የነበሩ ጠገቡ
መች ጎድሎብኝ ያውቃል አንተን ተደግፌ
በእጆችህ በረከት ተሞልቷል መዳፌ
አዝ--------------------//
እግዚአብሔር ይገላል እንዲሁም ያድናል
የኃይለኞችን ክንድ ሰብሮ ይታደጋል
መካኒቱ ሐና ወለደች ሰባት
ሥራህ ይደንቀኛል በቀን በሌሊት
አዝ--------------------//
ምስኪኑን ከጉድፍ ያነሳል ከምድር
ይዘረጋለታል የክብሩን ወንበር
ተመከረ ልቤ ሐናን ተመልክቶ
እግዚአብሔር ለጋስ ነው ለጠበቀው ከቶ
← መዝሙር