ልመናዮን ስማኝ

ልመናዬን ስማኝ ቃሌን አድምጠኝ
እውነተኛ አምላክ ሰላምህን ስጠኝ
ክርስቲያኖች ሁሉ ትእዛዙን አክብሩ
ምስጋናን አቅርቡ ስገዱ ዘምሩ
የጌታን አመጣጥ ለዓለም ንገሩ
ደቀመዛሙርቱ ወንጌል አስተምሩ
አዝ ---
በመልካም የሚሄድ ጽድቅን የሚሰራ
የፈጣሪውን ስም በከንቱ የማይጠራ
ይጎበኛል በምድር ከሰማዩ ስፍራ
በቀኝ ይቀመጣል ከቅዱሳን ጋራ
አዝ ---
ስለጠላቶቼ በጽድቅ ምራኝ
በጦር ቃል ከበቡኝ ተሳለቁብኝ
መሐሪ ይቅር ባይ መጠጊያ ሁነኝ
አንተ በቸርነትህ ይቅርታ ስጠኝ
← መዝሙር