ማመን እግዚአብሔር አንተን ማመን

ማመን እግዚአብሔር አንተን ማመን በአንተ መታመን
እጅግ ማትረፍ ነው በህይወት ዘመን
አላየሁም ፍፁም ሲጠፋ ሲባክን
ባንተ የታመነ ዘሩ እህል ሲለምን
የጥያቄው መልስ ተሟልቶ መሻቱ
አይተዋል ዓይኖቼ ተባርኮለት ቤቱ
አዝ.........................
የምታመንብህ መሸሸጊያ አለቴ
የደህንነቴ ቀንድ ሀይልና ብርታቴ
በቃልህ ስታመን ደግሞም በስምህ
ድል ከእኔ ጋር ነው አበርትቶኝ ክንደህ
አዝ.........................።
አይቻለሁ ቀኝህ ዳግም ስትረዳኝ
የእጅህ በረከት ሲትረፈረፍልኝ
ባዶ አይመለስም የተዘረጋ እጄ
በፀጋህ ይደምቃል ጓዳዬና ደጄ
አዝ.........................
ጓዳዬ ቢጎድል ያሰብኩት ባይሞላ
አትቅበዘበዝም ነፍሴ አንተን ጥላ
አምናለሁ ይሞላል ድካሜ ጉድለቴ
በአንተ ይፈጸማል ምኞቴ መሻቴ
አዝ......................
ስምህ ከደገፋት ከሆናት ከፍታ
ወዴት ትሄዳለች ነፍሴ አንተን ትታ
ጌታዬ አምላኬ ጉልበቴ እልሃለሁ
በሙላት በጉድለት እከተልሃለሁ
አዝ........................
‘’ ዲ.ን ዳንኤል ተካ እና ቀሲስ ብሩክ አስማረ
ዘማሪ ዲ.ን ዘማሪ ሳምሶን ነጋሽ
← መዝሙር