ማን እንደእርሱ
✦
ማን እንደ እርሱ እንደ እግዚአብሔር
ቸርነቱ ብዙ በሰማይ በምድር
ሞገድና ነፋስ የሚ ዘዙለት
አብርሕት ቀላያት የመሰከሩለት
ኅቱም መቃብርን ሳይከፍት የተነሣ
ነፍሳትን ያዳነ ከሲዖል አበሳ
አዝ ---
ፈዋሴ ድውያን ቸርነቱ ብዙ
የጸጋ ልብሳቸው ጽድቅን ለታረዙ
የተዋረዱትን ከፍ ከፍ የሚያደርግ
ለባልቴቷ ዳኛ ፈራጅ ለድኃ አደግ
አዝ ---
የጠፋውን አዳም ሊፈልግ የመጣ
ከባርነት ዓለም ከጽልመት ያወጣ
ብርሃን ዘበአማን ጨለማን ያራቀ
ሰውን ከራሱ ጋር ሞቶ ያስታረቀ
አዝ ---
በመከራ ሳሉ ሕዝቦቹን ያሰበ
ሥጋውና ደሙን ቆርሶ የመገበ
ከባቴ አበሳ ምሕረቱ የበዛ
ጌታችን እርሱ ነው የሁላችን ቤዛ
አዝ ---
ቸርነቱ ብዙ በሰማይ በምድር
ሞገድና ነፋስ የሚ ዘዙለት
አብርሕት ቀላያት የመሰከሩለት
ኅቱም መቃብርን ሳይከፍት የተነሣ
ነፍሳትን ያዳነ ከሲዖል አበሳ
አዝ ---
ፈዋሴ ድውያን ቸርነቱ ብዙ
የጸጋ ልብሳቸው ጽድቅን ለታረዙ
የተዋረዱትን ከፍ ከፍ የሚያደርግ
ለባልቴቷ ዳኛ ፈራጅ ለድኃ አደግ
አዝ ---
የጠፋውን አዳም ሊፈልግ የመጣ
ከባርነት ዓለም ከጽልመት ያወጣ
ብርሃን ዘበአማን ጨለማን ያራቀ
ሰውን ከራሱ ጋር ሞቶ ያስታረቀ
አዝ ---
በመከራ ሳሉ ሕዝቦቹን ያሰበ
ሥጋውና ደሙን ቆርሶ የመገበ
ከባቴ አበሳ ምሕረቱ የበዛ
ጌታችን እርሱ ነው የሁላችን ቤዛ
አዝ ---
✦