ማር ሚካኤል ልበል
✦
ማር ሚካኤል ልበል
ማር ሚካኤል ልበልህ
ባርከህ አሳደከኝ በቅኔ በዜማ መዝሙር አልሰስትም አባቴ ለአንተማ
ማር ሚካኤል ልበልህ
ባርከህ አሳደከኝ በቅኔ በዜማ መዝሙር አልሰስትም አባቴ ለአንተማ
ጅማሪዬ ታናሽ ያልበቃሁ ብሆንም
እንድጸና አውቃለሁ ከፊቴ ስትቀድም
ፍጻሜዬ እንዲያምር እንዲዋብ በቤትህ
አበርታኝ ልበርታ አጽናኝ ልጽና ልጅህ
ባህሩን ክፈለው በደረቅ እዳልፈው
እንዳልፈራ አበርታኝ እጄን በእጅህ ያዘው
እንድጸና አውቃለሁ ከፊቴ ስትቀድም
ፍጻሜዬ እንዲያምር እንዲዋብ በቤትህ
አበርታኝ ልበርታ አጽናኝ ልጽና ልጅህ
ባህሩን ክፈለው በደረቅ እዳልፈው
እንዳልፈራ አበርታኝ እጄን በእጅህ ያዘው
ከእንቅልፌ ያነቃኛል የደጅህ ደውል
በሌሊት መጥቼ ቤትህ እድውል
በሄድኩበት ሁሉ ካፌ አትነጠልም
የማር ወለላ ነው ሚካኤል ያንተ ስም
ማር ሚካኤል ስልህ ማር ማር አለው አፌ
መውደዴ እውነት ነው በምልጃህ ተርፌ
በሌሊት መጥቼ ቤትህ እድውል
በሄድኩበት ሁሉ ካፌ አትነጠልም
የማር ወለላ ነው ሚካኤል ያንተ ስም
ማር ሚካኤል ስልህ ማር ማር አለው አፌ
መውደዴ እውነት ነው በምልጃህ ተርፌ
በሞቱ ቀጠሮ ሠርግ የደገስክለት
ምና ባህራን ስታተርፈው ከሞት
ዛሬም ታምርህን ትድግናህን አይተው
ብዙዎች ይሉሀል ሚካኤል ሙት አንሳው
ረዳኤ ምንዱባን በስደት ደጋፊ
ከክፉ ከልለህ በድል አሳላፊ
ምና ባህራን ስታተርፈው ከሞት
ዛሬም ታምርህን ትድግናህን አይተው
ብዙዎች ይሉሀል ሚካኤል ሙት አንሳው
ረዳኤ ምንዱባን በስደት ደጋፊ
ከክፉ ከልለህ በድል አሳላፊ
አለቱን ከፍለህው በበትረ መስቀል
ከጭንጫው ሰጠኸን ማርና ጸበል
ቀድሞ ለእስራኤል ያኔ እንዳደረከው
ያን የሰማነውን ዛሬ ሆኖ አየነው
የብርሃኑን አምድ ፋና ተከትለን
ከቅዱሳን ስፍራ ዛጅርማኤል ደረስን
ከጭንጫው ሰጠኸን ማርና ጸበል
ቀድሞ ለእስራኤል ያኔ እንዳደረከው
ያን የሰማነውን ዛሬ ሆኖ አየነው
የብርሃኑን አምድ ፋና ተከትለን
ከቅዱሳን ስፍራ ዛጅርማኤል ደረስን
ከእንቅልፌ ያነቃኛል የደጅህ ደውል
በሌሊት መጥቼ ቤትህ እድውል
በሄድኩበት ሁሉ ካፌ አትነጠልም
የማር ወለላ ነው ሚካኤል ያንተ ስም
ማር ሚካኤል ስልህ ማር ማር አለው አፌ
መውደዴ እውነት ነው በምልጃህ ተርፌ።
በሌሊት መጥቼ ቤትህ እድውል
በሄድኩበት ሁሉ ካፌ አትነጠልም
የማር ወለላ ነው ሚካኤል ያንተ ስም
ማር ሚካኤል ስልህ ማር ማር አለው አፌ
መውደዴ እውነት ነው በምልጃህ ተርፌ።
✦