ማርያም ደስ ይበልሽ

ማርያም ደስ ይበልሽ በገብርኤል ሰላም
በአንቺ ስለአደረ የዓለም ሁሉ ጌ
የአምላክ ቸርነቱ ፈቃዱ ሲሆን
ጨለማ ተገፎ ሲወጣ ብርሃን
አዝ ---
መድኃኒት ሲመጣ ሰይጣን እንዳፈረ
የዜናው አብሣሪ ገብርኤል ነበረ
አዝ ---
ድንግል ተቀምጣ በቤተመቅደስ
ሐርና ወርቁን አስማም ስትፈትል
አዝ ---
ገብርኤል ዜናዊ ሐዲስ
የአምላክ መወለድ ሥጋ በመልበስ
አዝ - - -
ገብርኤል ሲያበስራት ድንግል ስትሰማ
በእርሷ ላይ አደረ በመንክር ግርማ
አዝ ---
እውነተኛ መልአክ መሆኑን ስላየች
ይሁንልኝ ብላ ቃሉን ተቀበለች
← መዝሙር