ማርያም ድንግል እንወድሻለን

ማርያም ድንግል እንወድሻለን
የሕይወትን ምግብ ሰጥተሽናልና
የሕይወትን መጠጥ ሰጥተሽናልና
ላንቺ ይገባል ክብርና ምስጋና
በዚያች በክፉ ቀን በክህደት ወራት
በክንፎችሽ ጋርደሽ ሰውረሽ ከመዓት
ቃሉን ተመግበን ፍቅሩን ተረድተን
ልጆችሽ ለመሆን ምልጃሽ ረዳን ማርያም እንወድሻለን
አዝ----
እኛ ልጆችሽን በፍቅር ሰብስበሽ
በሐዘን በደስታ ከኛ ጋር ሆነሽ
ማዕበሉ ቆሞ ወጀቡን አልፈን
በልጅሽ ቸርነት ለዚች ቀን በቃን ማርያም እንወድሻለን
አዝ---
እናቅርብ ምስጋና እንዘምር ዝማሬ
ለነገስታት ንጉሥ ለማህጸንሽ ፍሬ
ድንግል የአምላክ እናት እናወድስሽ
ቃላት አይገልጸውም ልዩ ነው ፍቅርሽ ማርያም እንወድሻለን
አዝ--
← መዝሙር