ማርያም ድንግል ጸልይ

ማርያም ድንግል ጸልይ ጸልይ
ጸልይ ድንግል ለመላው አለም
እንዲያገኝ ሰላም
ጸልይ ድንግል ማርያም ለመላው አለም
የምህረት ቃል ኪዳን ገብቶልሻልና ካንቺ የተወለድው መድኃኔዓለም
ቃል እንደ ገባለት ቀድሞ ለአዳም
ተሰቅሎ ያድነው ዘንድ በፍቅሩ ፍጹም
የህየውት መሰላል ነሽ የዳዊት መሰንቆ የሰሎሞን አክሊል የሴም ቡራኬው
የሙሴ ጽላት ነሽ የአዳም ተስፋው
ከገነት በወጣ ጊዜ ዞሮ መግቢያው
በስደተኛው ወር ወደ አንቺ ተልኮ እንዳመሰግነሽ ገብርኤል በቃሉ
ያመሰግኑሻል ትውልዱም በሙሉ
እንደ ተጻፈ በወንጌሉ ብጽህት እያሉ
የነቢያት ትንቢት የቅዱሳን ተስፋ ያቺ የጽድቅ በር ሕዝቅኤል ያያት
የአሮን በትር እፀ መድኃኒት
አማልጅን ኪዳነ ምህረት ዳግመኛ እንዳንሞት
← መዝሙር