ማርያም ማርያም ብዬ

ማርያም ማርያም ብዬ ስምሽን ልጥራዉ
አይደክመኝም እኔ ብደጋግመዉ
አሁንም ጠራሁሽ አላስችልህ ቢለኝ
2
አውቀዋለሁ ስምሽን እናቴ ስትወልደኝ
ገና በማሕፀን በእናቴ ምጥ ቀን
ደጋግሜ ሰማሁ ሲጠሩ ስምሽን
በሰከንዳት እድሜ የማውቃት አንዲት ቃል
ልቤ ላይ ያለው ስም ማርያም ማርያም
ይላል/2
ማርያም ማርያም
ማርያም ማርያም ብዬ ስምሽን ልጥራዉ
አይደክመኝም እኔ ብደጋግመው
አሁንም ጠራሁሽ አላስችልህ ቢለኝ
2
አውቀዋለሁ ስምሽን እናቴ ስቶልደኝ
ሔዋን ምጧ ቀሎ ልጆቿን ታቀፈች
በአማላጅነትሽ እናቴም ታመነች
በተወለድኩባት በመጀመሪያው ቀን
ስምሽን እየሰማሁ ወጣሁ
ከማሕፀን/2
ማርያም ማርያም
ማርያም ማርያም ብዬ ስምሽን ላጥራዉ
አይደክመኝም እኔ ብደጋግመዉ
አሁንም ጠራሁት አላስችልህ ቢለኝ
አውቀዋለሁ ስምሽን እናቴ ስትወልደኝ
ከቃል ኪዳን ስም ጋር አደኩኝ አብሬ
ምልጃሽ ሳይለየኝ አለሁ እስከዛሬ
የሕይወቴን ፊደል ካንቺ ላይ ቆጠርኩኝ
በልጅሽ ታምኜ ዳግም ተወለድኩኝ/2
ማርያም ማርያም
ማርያም ማርያም ብዬ ስምሽን ልጥራው
አይደክመኝም እኔ ብደጋግመው
አሁንም ጠራሁሽ አላስችልህ ቢለኝ
አውቀዋለሁ ስምሽን እናቴ ስትወልደኝ
ማርያም ማርያም
የክፉ ቀን ስንቄ ያዘልኩሽ በልቤ
የሕይወቴ ምግብ የእንጀራ መሶቤ
እንደ ትናትና ዛሬም እጠራሻለሁ
የመስቀል ስር ክብሬን እንዴት እረሳለሁ
የመስቀል ስር ክብሬን እንዴት እረሳዋለሁ
ማርያም ማርያም
ማርያም ማርያም ብዬ ስምሽን ልጥረው
አይደክመኝም እኔ ብደጋግመው
አሁንም ጠራሁሽ አላስችልህ ቢለኝ
አውቀዋለሁ ስምሽን እናቴ ስትወልደኝ
← መዝሙር