ማርያም

ማርያም ደስ ይበልሽ በገብርኤል ሰላምታ
ባንቺ ስላደረ የዓለም ሁሉ ጌታ
አዝ --------------
የአምላክ ቸርነቱ ፈቃዱ ሲሆን
ጨለማው ተገፎ ሲወጣ ብርሃን
አዝ --------------------
ድንግል ተቀምጣ በቤተ መቅደስ
ሐር ወር አስማምታ ስትፈትል ንግሥት
አዝ ------------------
ገብርኤል ዜናዊ ሐዲስ
የአምላክን መወለድ ሥጋ በመልበስ
አዝ ---------------
ገብርኤል ሲያበስራት ድንግል ስትሰማ
በእርስዋ ላይ አደረ የመለኮት ግርማ
አዝ --------
እውነተኛ መልአክ መሆኑን ስላየች
ይሁንልኝ ብላ ቃሉን ተቀበለች
← መዝሙር