መቼነው ጌታ
✦
መቼ ነው ጌታ ኧረ መቼ ነው
መቼ ነው ጌታዬ እንደቃልህ የሚሆን ጉዞዬ፪
መቼ ነው ጌታዬ እንደቃልህ የሚሆን ጉዞዬ፪
አልተማርኩም አልል አስተምረኸኛል፪
ቃለህን እንደ ወተት አጠጥተኸኛል፪
ቃለህን እንደ ወተት አጠጥተኸኛል፪
መቼ ነው ጌታ ኧረ መቼ ነው
መቼ ነው ጌታዬ እንደቃልህ የሚሆን ጉዞዬ፪
መቼ ነው ጌታዬ እንደቃልህ የሚሆን ጉዞዬ፪
የታል አኗኗሬ አንተን የሚመስለው፪
በልማድ ሕይወት ነው የምመላለሰው፪
በልማድ ሕይወት ነው የምመላለሰው፪
መቼ ነው ጌታ ኧረ መቼ ነው
መቼ ነው ጌታዬ እንደቃልህ የሚሆን ጉዞዬ፪
መቼ ነው ጌታዬ እንደቃልህ የሚሆን ጉዞዬ፪
ይህ አንደበቴማ በቃልህ ሠልጥኗል፪
ልቦናዬ ካንተ ከፊትህ ኮብልሏል፪
ልቦናዬ ካንተ ከፊትህ ኮብልሏል፪
መቼ ነው ጌታ ኧረ መቼ ነው
መቼ ነው ጌታዬ እንደቃልህ የሚሆን ጉዞዬ፪
መቼ ነው ጌታዬ እንደቃልህ የሚሆን ጉዞዬ፪
አንተን እንደማውቅህ አብዝቼ ባወራ፪
የተዘራው ሁሉ ፍሬ አላፈራ፪
የተዘራው ሁሉ ፍሬ አላፈራ፪
መቼ ነው ጌታ ኧረ መቼ ነው
መቼ ነው ጌታዬ እንደቃልህ የሚሆን ጉዞዬ፪
መቼ ነው ጌታዬ እንደቃልህ የሚሆን ጉዞዬ፪
እዘንልኝና መንገዴን አቅናልኝ፪
የአመጻ ሥራዬን በደሌን ተውልኝ፪
የአመጻ ሥራዬን በደሌን ተውልኝ፪
መቼ ነው ጌታ ኧረ መቼ ነው
መቼ ነው ጌታዬ እንደቃልህ የሚሆን ጉዞዬ፪
መቼ ነው ጌታዬ እንደቃልህ የሚሆን ጉዞዬ፪
ቃልህ እንዳይሰደብ በእኔ ድካም፪
አርመው እርሻህን መድኃኔዓለም፪
አርመው እርሻህን መድኃኔዓለም፪
መቼ ነው ጌታ ኧረ መቼ ነው
መቼ ነው ጌታዬ እንደቃልህ የሚሆን ጉዞዬ፪
መቼ ነው ጌታዬ እንደቃልህ የሚሆን ጉዞዬ፪
ከእስራቴ አውጥተህ ነፃነት ስጠኝ፪
በቀኝህ አቁመህ ጌታዬ ሆይ ባርከኝ፪
በቀኝህ አቁመህ ጌታዬ ሆይ ባርከኝ፪
መቼ ነው ጌታ ኧረ መቼ ነው
መቼ ነው ጌታዬ እንደቃልህ የሚሆን ጉዞዬ፪
መቼ ነው ጌታዬ እንደቃልህ የሚሆን ጉዞዬ፪
ኃጢያት ሞትን ወልዶ እንዳያጠፋኝ፪
የብርሃን ፊትህ ይገለጽልኝ፪
የብርሃን ፊትህ ይገለጽልኝ፪
✦