መናን አውርዶ እሳት አብርዶ
✦
መናን አውርዶ እሳት አብርዶ
ሚካኤል መራን ደመና ጋርዶ ፪
ሚካኤል መራን ደመና ጋርዶ ፪
ነፀብራቃዊው ሚካኤል
አምደ ብርሃን ሚካኤል
ነፃ ያወጣ ሚካኤል
ህዝበ እስራኤልን ሚካኤል
ሌሊቱን ብርሃን እያደረክ
ምራን እኛንም ወደ አምላክ
መናን አውርዶ እሳት አብርዶ
ሚካኤል መራን ደመና ጋርዶ ፪
ሩሩህ መላዕክ ሚካኤል
የአፎምያ አባት ሚካኤል
ፈጥነህ የምትደርስ ሚካኤል
በጭንቀት ላሉ ሚካኤል
ጠላት ዲያብሎስ እንዳይጥለን
ቅዱስ ሚካኤል አትለየን
አምደ ብርሃን ሚካኤል
ነፃ ያወጣ ሚካኤል
ህዝበ እስራኤልን ሚካኤል
ሌሊቱን ብርሃን እያደረክ
ምራን እኛንም ወደ አምላክ
መናን አውርዶ እሳት አብርዶ
ሚካኤል መራን ደመና ጋርዶ ፪
ሩሩህ መላዕክ ሚካኤል
የአፎምያ አባት ሚካኤል
ፈጥነህ የምትደርስ ሚካኤል
በጭንቀት ላሉ ሚካኤል
ጠላት ዲያብሎስ እንዳይጥለን
ቅዱስ ሚካኤል አትለየን
መናን አውርዶ እሳት አብርዶ
ሚካኤል መራን ደመና ጋርዶ ፪
ሚካኤል መራን ደመና ጋርዶ ፪
የሚቃወሙን ሚካኤል
በእርሱ እራቀልን
ጠላቶቻችን ሚካኤል
ተሽነፉልን ሚካኤል
የማንችለውን እያስቻለን
ለዚህ አበቃን እየረዳን
በእርሱ እራቀልን
ጠላቶቻችን ሚካኤል
ተሽነፉልን ሚካኤል
የማንችለውን እያስቻለን
ለዚህ አበቃን እየረዳን
መናን አውርዶ እሳት አብርዶ
ሚካኤል መራን ደመና ጋርዶ ፪
ሚካኤል መራን ደመና ጋርዶ ፪
ወደ ሞት ሲሄድ ሚካኤል
ደብዳቤ ይዞ ሚካኤል
ደጉ ባህራን ሚካኤል
ከንጉሱ ታዞ ሚካኤል
ቅዱስ ሚካኤል በረድኤት
ሞቱን ወድ ህይወት ለወጠለት
ደብዳቤ ይዞ ሚካኤል
ደጉ ባህራን ሚካኤል
ከንጉሱ ታዞ ሚካኤል
ቅዱስ ሚካኤል በረድኤት
ሞቱን ወድ ህይወት ለወጠለት
መናን አውርዶ እሳት አብርዶ
ሚካኤል መራን ደመና ጋርዶ ፪
ሚካኤል መራን ደመና ጋርዶ ፪
✦