መነሻዬ አንተ ነህ

መነሻዬ አንተ ነህ መድራሻዬም ጌታ
እግዚአብሔር ለእኔ የህይወቴ አለኝታ
እኔ ማን ነኝ ብዬ ስጠይቅ እራሴን
ሁሉንም ከአንተ ዘንድ አገኘሁት መልሴን
ይገርመኛል ሁሌም ስራህን ሳስበው
እንዲህ በአጭር ዘመን ለእኔ ባደረከው
ለዚህ ቀን መብቃቴ በአንተ ነው መቆሜ
ጌታዬ ያላንተማ መች ይገኛል እድሜ
አዝ..............
ስርቅህ ሳትርቀኝ ቀርበህ ከእስትንፋሴ
ቀንበሬን ሰብረኸው ቀረ ማጎንበሴ
መከታ ለሆንከኝ ለህይወቴ ጥላ
ዘመኔን ልፈፅም ሳላይ ከአንተ ሌላ
አዝ...............
ከቤትህ እንዳሉት ልሁን አገልጋይህ
እያልኩኝ እትቁጥረኝ አባቴ እንደ ልጅህ
በፍቅር ተቀበልከኝ መች ልብህ ሊጨክን
ዳግም ልጄ ብለህ ቀየርክልኝ ልብሴን
አዝ..............
አይሆንም እያልኩኝ የወሰንኩት ነገር
ሲሆን አይቻለሁ አንተ ስትናገር
ድምፅህን ለመስማት ጆሮ አለው ባህር
ወጀቡም ፀጥ ይላል ስለቃልህ ክብር
አዝ...............................................
‘’ ዲ.ን መምህር ዳንኤል ተካ
‘’ ቀሲስ መምህር ብሩክ አስማረ
ዘማሪ ዲ.ን ልዑልሰገድ ጌታቸው
← መዝሙር