መርኣዊ ሰማያዊ

መርዓዊ ሰማያዊ
ለእመ ገብረ በዓለ ኧኸ
መድኃኒዓለም ነው የሰማይ ሙሽራ
ከሰርጉ ለመግባት ተነሱ በተራ
..........
የሾህ አክሊል ደፍቶ የተሞሸረው
ቤተ ክርስቲያንን በደሙ የዋጀው
ኢየሱስ ክርስቶስ እርሱ ነው ሙሽራ
በመስቀሉ ብርሃን ለሁሉ ያበራ
..............
ሚዜው ደስ ብሎታል መጥምቁ ዮሐንስ
ሙሽራዋን ይዞ ወደ እራሷ ሲደርስ
ደቀ መዛሙርቱም ምንም አላዘኑ
ከሙሽራው ጋር አብረው ስለሆኑ
.............
ከማሰሮው ጋራ መብራት እንዳትረሱ
ይመጣል በድንገት ሙሽራው ንጉሱ
ቢዘገይም እንኳን አይቀርም ይመጣል
ወደ ሰማዩ ሰርግ ኑ ግቡ ይለናል
...............
አእላፍ መላእክት በሰማይ ቤት አሉ
ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ኃያል ነህ እያሉ
የቃናዋ እንግዳ ድንግል ማርያም
በሰርጉ ቤት አለች ድንግል ማርያም
← መዝሙር