መስቀል ተመርኩዘን

መስቀል ተመርኩዘን ወንጌል ተጫምተን
ሃይማኖትን ሰብከን በክርስቶስ አምነን
ማን ያሸንፈናል እኛ ክርስቲያን
ክርስቶስ አለልን
ንግሥቲቷ ዕሌኒ በጣም የደለች
በዕጣን ጢስ ተመር መስቀሉን አገኘች
መስቀሉን ስትፈልግ ኪራኮስን ይዛ
መስቀሉን አገኘች የዓለሙን ቤዛ
አዝ . . .
ሙንም ተነሥተው ያመሰገኑት
ዕፀ መስቀሉ ነው የእኛ መድኃኒት
መስቀል ምርኩዛችን ጎዳና ወንጌል
ወደገነት እንጂ አንሔድም ሲዖል
አዝ . . .
ንም ንወድሶ ለእፀ መስቀል
የተሸከመውን የአምላክን ቃል
ንም ንወድሳ ለማርያም ድንግል
አክሊለ ምዕመናን ምክኃ ደናግል
አዝ . . .
← መዝሙር