መስቀሉን ተሸክመን

መስቀሉን ተሸክመን በእምነት እንራመድ
ለሰማያዊው ክብር እንጓዝ ወደእርሱ ዘንድ
እግዚአብሔር አብ ላከ አንድያ ልጁን
እርሱ ወዷልና እንዲሁ ዓለሙን
አዝ . . .
ከኃጢያት ያዳንከን ደምህን አፍስሰህ
የሰላም ባለቤት አምላክ አንተ ነህ
አዝ . . .
ይቅር ባይ መሐሪ ሰው ወዳጅ አምላክ
በመንፈስህ አጽናን እንዳንወክ
አዝ . . .
አንተ ነህ ሕይወት መንገድና እውነት
አብቃን የእኛ ጌ ለዘላለም ሕይወት
አዝ . . .
← መዝሙር