መጽሐፍ ቅዱስን
✦
መጽሐፍቅዱስን ሁሉም ያነበዋል
ምእራፍና ቁጥሩን ሁሉም ይጠቅሰዋል
በዚህ ብቻ አይበቃም ተርጓሚ ያሻዋል፪
እንደፈቃዳችን ብንተረጉመው፪
በውጥን የሚልቀው ስህተቱ ብዙ ነው፪
ከቶ በሰው ፈቃድ ትንቢት እንዳልመጣ ፪
ይነግረናል መጽሐፍ ከሕግ እንዳንወጣ
ይመክረናል መጽሐፍ ከሕግ እንዳንወጣ
እንጠይቅ መምህራን ያሉት በደረጃ ፪
እናንብብ መጽሐፍት ይሁኑን ማስረጃ፪
ምእራፍና ቁጥሩን ሁሉም ይጠቅሰዋል
በዚህ ብቻ አይበቃም ተርጓሚ ያሻዋል፪
እንደፈቃዳችን ብንተረጉመው፪
በውጥን የሚልቀው ስህተቱ ብዙ ነው፪
ከቶ በሰው ፈቃድ ትንቢት እንዳልመጣ ፪
ይነግረናል መጽሐፍ ከሕግ እንዳንወጣ
ይመክረናል መጽሐፍ ከሕግ እንዳንወጣ
እንጠይቅ መምህራን ያሉት በደረጃ ፪
እናንብብ መጽሐፍት ይሁኑን ማስረጃ፪
✦