ምደረ ቀራኒዮ
✦
ምደረ ቀረንዮ ምደረ ጎልጎታ
መድኃኒት ክርስቶስ በአንቺ ተንገላታ፪
መስክሪ አንቺ ምድር ግኡዚቷ ሥፍራ
መድኃኒት ክርስቶስ ያየብሽን መከራ፪
ደሙ እንደውኃ ሲፈስ መስቀሉ2/
በቀራንዮ ቦታ መከራውን ሲያይ፪
ፀሐይ ከለከለች ደማቅ ብርሃኗን ፪
ለመሸፈን ብላ የአምላክን እርቃን፪
በመስቀል ተሰቅሎ ፍቅሩን ገለጸው ፪
በመስቀል ላይ ሆኖ ተጠማሁ እያለ ፪
የሾህ አክሊል ደፍቶ ቀራንዮ ዋለ ፪
እጆቹን እግሮቹን በችንካር ተመተው፪
ቸሩ መድኃኔዓም እባክህ ማረን፪/
ደካሞች ነንና እንዳንቀር ጠፍተን፪
በቆረሰከው ስጋ ባፈሰሰከው ደም፪
አቤቱ ተራዳ እስከ ዘላለም፪
መድኃኒት ክርስቶስ በአንቺ ተንገላታ፪
መስክሪ አንቺ ምድር ግኡዚቷ ሥፍራ
መድኃኒት ክርስቶስ ያየብሽን መከራ፪
ደሙ እንደውኃ ሲፈስ መስቀሉ2/
በቀራንዮ ቦታ መከራውን ሲያይ፪
ፀሐይ ከለከለች ደማቅ ብርሃኗን ፪
ለመሸፈን ብላ የአምላክን እርቃን፪
በመስቀል ተሰቅሎ ፍቅሩን ገለጸው ፪
በመስቀል ላይ ሆኖ ተጠማሁ እያለ ፪
የሾህ አክሊል ደፍቶ ቀራንዮ ዋለ ፪
እጆቹን እግሮቹን በችንካር ተመተው፪
ቸሩ መድኃኔዓም እባክህ ማረን፪/
ደካሞች ነንና እንዳንቀር ጠፍተን፪
በቆረሰከው ስጋ ባፈሰሰከው ደም፪
አቤቱ ተራዳ እስከ ዘላለም፪
✦