ሚካኤል ኃያል ሚካኤል

✦
ሚካኤል ኃያል ሚካኤል
ከጠላታችን ነፃ አወጣን
ከአምላክ ተልኮ እረዳን፤ ፪
ሌሊቱን በብርሃን ቀኑን በደመና
መርተህ አወጣኸን ከግብፅ መከራ
የእግዚአብሔር መልአክ ርኅሩህ
ሚካኤል ሆይ ናና ዛሬም ታደገኝ
ሚካኤል ኃያል ሚካኤል
ከጠላታችን ነፃ አወጣን
ከአምላክ ተልኮ እረዳን፤ ፪
በፈተና ጊዜ ፈጥነህ ድርሰሃል
ሀዘንን መከራን ከእኛ አርቀሀል
እንዘምራለን ለታላቁ ክብርህ
ታጋሽ እና ብርቱ ግሩም መልአክ
ሚካኤል ኃያል ሚካኤል
ከጠላታችን ነፃ አወጣን
ከአምላክ ተልኮ እረዳን፤ ፪
ሳጥናኤል ከክብሩ ትዕቢቱ ቢሽረው
ሚካኤል ተሾመ ዘወትር ይኖራል
በሚፈሩት ዙሪያ ዘወትር ይኖራል
ከዲያቢሎስ ውጊያ ሕዝቡን ይታደጋል
ሚካኤል ኃያል ሚካኤል
ከጠላታችን ነፃ አወጣን
ከአምላክ ተልኮ እረዳን፤ ፪
✦
← መዝሙር