ሚካኤል ሐመልማለ ወርቅ
✦
ሚካኤል ሐመልማለ ወርቅ ፪ ልብሱ ዘመብረቅ ፪
ሚካኤል ሐመልማለ ወርቅ የወርቅ ልምላሜ ፪
ና ፫ ስለምንህ ቆሜ
ና ፫ ስለምንህ ቆሜ
ገብርኤል ሊቀ መላእክት ፪
ሠለስቱ ደቂቅን ያወጣ ከእሳት
ሠለስቱ ደቂቅን ያወጣ ከእሳት
በሠለስቱ ደቂቅ ናቡከደነጾር ተቆጣ
እሳቱ ነደደ ነበልባሉ ወጣ
ግን ኃያል ገብርኤል ሊያድናቸው መጣ
እሳቱ ነደደ ነበልባሉ ወጣ
ግን ኃያል ገብርኤል ሊያድናቸው መጣ
ገብርኤል ሊቀ መላእክት ፪
ሠለስቱ ደቂቅን ያወጣ ከእሳት
ሠለስቱ ደቂቅን ያወጣ ከእሳት
ሠለስቱ ደቂቅ ይባርክዎ ለእግዚአብሔር
ስቡሕኒ ውእቱ ወልዑልኒ ውእቱ ብለው
ምስጋና አቀረቡ ከእሳቱ ላይ ሆነው
ስቡሕኒ ውእቱ ወልዑልኒ ውእቱ ብለው
ምስጋና አቀረቡ ከእሳቱ ላይ ሆነው
ገብርኤል ሊቀ መላእክት ፪
ሠለስቱ ደቂቅን ያወጣ ከእሳት
ሠለስቱ ደቂቅን ያወጣ ከእሳት
ራጉኤል ሊቀ መላእክት ፪
እመ ኀበ ላዕል ወረደ ፪
እመ ኀበ ላዕል ወረደ ፪
መጋቤ ብርሃናት አንሶሳዌ ፋና
ራጉኤል ና ፭ አማላጅ ነህና
ራጉኤል ና ፭ አማላጅ ነህና
ራጉኤል ሊቀ መላእክት ፪
እመ ኀበ ላዕል ወረደ ፪
እመ ኀበ ላዕል ወረደ ፪
ዑራኤል ሊቀ መላእክት ፪
ለዕዝራ ያጠጣህ ጽዋዐ ሕይወት
ለዕዝራ ያጠጣህ ጽዋዐ ሕይወት
በዓለም ፈተና በስቃይ ኩነኔ
ስባዝን ስጨነቅ ስጠበብ ወይ እኔ
ዑራኤል የእኔ ኃይል ቁምልኝ ከጎኔ
ስባዝን ስጨነቅ ስጠበብ ወይ እኔ
ዑራኤል የእኔ ኃይል ቁምልኝ ከጎኔ
ዑራኤል ሊቀ መላእክት ፪
ለዕዝራ ያጠጣህ ጽዋዐ ሕይወት
ለዕዝራ ያጠጣህ ጽዋዐ ሕይወት
✦