ምክሐ ምእመናን (መምህረ ወንጌል)

ምክሐ ምእመናን (መምህረ ወንጌል)
መምህረ ወንጌል ምክሐ ምእመናን ሰላማ ከሣቴ ብርሃን
ገናና ስሙን ልትሸከም የጠራህ መድኃኔ አለም
ፈጣሪ የላከህ ለድህነታችን
አምደ ሃይማኖት ብጹዕ አባታችን
የወንጌል አርበኛ ሐዋርያ
ሁሌም ታነሳለች ስምህን ኢትዮጵያ
አዝ----
ኢትዮጵያን ርስትህ አድርገህ
ለስብከተ ወንጌል በስደት መኖርን መርጠህ
ስላመጣህላት ስርዓተ ክህነትን
ታወድስሀለች አሃቲ ቤተክርስቲያን
አዝ----
እንደ ጳውሎስ ሐዋርያ
እንደ ማርቆስ መምህር ዘእስክንድሪያ
ደግሞም እንደ ጴጥሮስ መምህረ ሐዲስ
ክብርህ ከፍ ያለ ነው አባ ፍሬምናጦስ
አዝ----
← መዝሙር