ምን ሰማህ ዮሐንስ
✦
ምን ሰማህ ዮሐንስ /በማሕፀን ሳለህ /፪
ሕፃን ሆነህ ነቢይ /ለክብር የተጠራህ /፪
እንደ እንቦሳ ጥጃ/ያዘለለህ ደስታ/፪
ምን ዓይነት ድምፅ ነው /ምን አይነት ሰላምታ/፪
ሕፃን ሆነህ ነቢይ /ለክብር የተጠራህ /፪
እንደ እንቦሳ ጥጃ/ያዘለለህ ደስታ/፪
ምን ዓይነት ድምፅ ነው /ምን አይነት ሰላምታ/፪
ከተፈጥሮ በላይ ያሰገደህ ክብር
እንዴት ቢገባህ ነው/የእናታችን ፍቅር /፪
ሌላ ድምፅ አልሰማም ከእንግዲህ በኋላ
ለውጦኛልና /የሰላምታ ቃሏ /፪
አዝ......
በረሃ ያስገባህ ለብዙ ዘመናት
ምን ያለ ራዕይ /እንዴት ያለ ብሥራት/፪
አንደ አዲስ ምስጋና ስልቱ የተዋበ
ተደምጦ የማያውቅ/ጭራሽ ያልታሰበ /፪
አዝ.......
ከሴት ከተገኙ ከደቂቀ አዳም
ድንግል ስለሆነ /በሕይወቱ ፍጹም/፪
ከማሕፀን ሳለ ተመርጦ በጌታ
ለማዳመጥ በቃ የኪዳን ሰላምታ/፪
እንዴት ቢገባህ ነው/የእናታችን ፍቅር /፪
ሌላ ድምፅ አልሰማም ከእንግዲህ በኋላ
ለውጦኛልና /የሰላምታ ቃሏ /፪
አዝ......
በረሃ ያስገባህ ለብዙ ዘመናት
ምን ያለ ራዕይ /እንዴት ያለ ብሥራት/፪
አንደ አዲስ ምስጋና ስልቱ የተዋበ
ተደምጦ የማያውቅ/ጭራሽ ያልታሰበ /፪
አዝ.......
ከሴት ከተገኙ ከደቂቀ አዳም
ድንግል ስለሆነ /በሕይወቱ ፍጹም/፪
ከማሕፀን ሳለ ተመርጦ በጌታ
ለማዳመጥ በቃ የኪዳን ሰላምታ/፪
✦