ምንም ሳትበድል

ምንም ሳትበድል ኃጢኣት ሳይኖርባት
አንድዬ ልጇን ሄሮድስ ሊገድልባት
ሀገር እንደሌለው ከሀገር ሲያሳድዳት ምን በድላ ይሆን
ምን ኃጢኣት ኖሮባት
የአዳም መዳኛ ድንግል ማርያም
አንድ ልጇን ይዛ ካረች በዓለም
ሄድሮስ ምቀኛ የዲያብሎስ ወዳጅ
ሊገድለው አስቦ የድንግልን ልጅ
መኟ ለእርሷ አዘነ ጨከነባት እንጂ
ስትሆን ለፍጥረት የዓለም አማላጅ
አዝ -------------
የሲና በረሃ እግሯን እየፈጀው
አንጀቷ ተርቦ ውኃ ጥም ሲፈጀው
መኟ ለእርሷ አዘነች የርሷን መንገላት
ሐሰቧ ለእርሱ ነው እንዳይገድሉባት
አዝ -------------
አቤት መከራሽ አቤት ስደትሽ
እኔ ልኝፈለው ወራዳው ልጅሽ
መሰደድ ያለብኝ እኔ ነበርኩኝ
የእግዚአብሔ@ርን ትእዛዝ የተላለፍኩኝ
አዝ -------------
← መዝሙር