ምሬሃለሁ በለኝ ስለ ድንግል ማርያም
✦
ምሬሃለሁ በለኝ ስለ ድንግል ማርያም
መሀሪው መድኃኒዓለም ይቅር ባይ እንዳንተ የለም (2×)
በሀጥያት ድንኳኖች ይብቃ መቀመጤ
የቀናውን መንፈስ አድሰው በውስጤ
የምህረት አይኖችህ ይዩኝ በይቅርታ
ስለ ድንግል ማርያም እስራቴን ፍታ
ቸል በማለቴ የደምህን ዋጋ
ተመልሼ ገባው ከጥፋት መንጋጋ
ሰላሜ ደፍርሶ ተቅበዝባዥ ሆኛለው
ስለ እናትህ ብለህ ማረኝ እልሃለው
ስለ ድንግል ማርያም ማረኝ እልሃለው
በከንቱ መሻቴ ስጋ ነፍሴን ቀብሮ
አቅም አጥቻለው አጥንቴ ተሰብሮ
ከበረዶ ይልቅ ነጭ እንድታደርገኝ
ስለ ድንግል ማርያም ከሀጥያቴ እጠበኝ
ስለ ድንግል ማርያም ምሬሃለሁ በለኝ
ከንፈሮቼን ከፍተህ ልቁም ለምስጋና
አንተን የጋረደኝ ጣርያ ይነሳና
አልብሰኝ ፅድቅህን ይቅር መራቆቴ
ስለ ድንግል ማርያም መልሰኝ ከቤቴ
ምሬሃለሁ በለኝ ስለ ድንግል ማርያም
መሀሪው መድኃኒዓለም ይቅር ባይ እንዳንተ የለም ፪
መሀሪው መድኃኒዓለም ይቅር ባይ እንዳንተ የለም (2×)
በሀጥያት ድንኳኖች ይብቃ መቀመጤ
የቀናውን መንፈስ አድሰው በውስጤ
የምህረት አይኖችህ ይዩኝ በይቅርታ
ስለ ድንግል ማርያም እስራቴን ፍታ
ቸል በማለቴ የደምህን ዋጋ
ተመልሼ ገባው ከጥፋት መንጋጋ
ሰላሜ ደፍርሶ ተቅበዝባዥ ሆኛለው
ስለ እናትህ ብለህ ማረኝ እልሃለው
ስለ ድንግል ማርያም ማረኝ እልሃለው
በከንቱ መሻቴ ስጋ ነፍሴን ቀብሮ
አቅም አጥቻለው አጥንቴ ተሰብሮ
ከበረዶ ይልቅ ነጭ እንድታደርገኝ
ስለ ድንግል ማርያም ከሀጥያቴ እጠበኝ
ስለ ድንግል ማርያም ምሬሃለሁ በለኝ
ከንፈሮቼን ከፍተህ ልቁም ለምስጋና
አንተን የጋረደኝ ጣርያ ይነሳና
አልብሰኝ ፅድቅህን ይቅር መራቆቴ
ስለ ድንግል ማርያም መልሰኝ ከቤቴ
ምሬሃለሁ በለኝ ስለ ድንግል ማርያም
መሀሪው መድኃኒዓለም ይቅር ባይ እንዳንተ የለም ፪
✦