ምስጋና አምልኮ

ምስጋና አምልኮ ስግደት ውዳሴ
ይገባል በሉ ሰዎች ለቅስት ስላሴ /2x/
ዘላለም አለም ቅዱስ ነህ
አምሳያ ወደር የሌለህ
መተማመኛ ሆነኸኛል
ስላሴ ባንተ ደስ ይለኛል
የታመነ ነው የተፈራ
የጽድቅን ፀሐይ የሚያበራ
አለሙ ፀንቷል በስላሴ
ትዘምርለት ለእርሱ ነፍሴ
ስምናት በጁ በመዳፉ
ሁሌም የርሱ ነው ሁሉ ሰልፉ
የእሳት መድረኮች ያሉት ጌታ
የማያልፍ ነው ማይረታ
አብርሀም አምኖ ተሰደደ
በእርጅናው ወራት ልጅ ወለደ
የተስፋውን ቃል ፈፀመለት
ስላሴ በሉ በቀን በሌሊት
← መዝሙር