ምስጋና እናቅርብ
✦
ምስጋና እናቅርብ በዕለተ ሰንበት
የሁሉ መገኛ ምድርን ላደረጋት፪
ሃሌ ሉያ፬ እንዘምር በአንድነት፪
የሁሉ መገኛ ምድርን ላደረጋት፪
ሃሌ ሉያ፬ እንዘምር በአንድነት፪
አምላክን አመስግኚ ምድር ተደሰቺ
የሁሉ መገኛ በመሆንሽ አንቺ፪
ሃሌ ሉያ ፬ ለምስጋና በርቺ፪
የሁሉ መገኛ በመሆንሽ አንቺ፪
ሃሌ ሉያ ፬ ለምስጋና በርቺ፪
ይሆናል ደስታሽ በጣም የሚማርክ
በቅጠል በአበባ ሲሸፍንሽ አምላክ፪
ሃሌ ሉያ ፬ ፈጣሪሽ ይባረክ፪
በቅጠል በአበባ ሲሸፍንሽ አምላክ፪
ሃሌ ሉያ ፬ ፈጣሪሽ ይባረክ፪
የዘራም ያልዘራም በዐይን ይጠግባሉ
አበባባ ፍሬ በአንቺ ላይ ሲኖሩ፪
ሃሌ ሉያ ፬ ይዘምር ሰው ሁሉ፪
አበባባ ፍሬ በአንቺ ላይ ሲኖሩ፪
ሃሌ ሉያ ፬ ይዘምር ሰው ሁሉ፪
ይህን ሁሉ ጸጋ ለአንቺ የሰጠው
ለሰንበት ባለቤት ምስጋና ይግባው፪
ሃሌ ሉያ፬ ስሙን እናንሳው፪
ለሰንበት ባለቤት ምስጋና ይግባው፪
ሃሌ ሉያ፬ ስሙን እናንሳው፪
✦