ምስጋና ላቅርብ ለስላሴ

ምስጋና ላቅርብ ለስላሴ
በእጁ በረከት ተማርካለች ነፍሴ
ምስጋና ላቅርብ ለስላሴ
ካለመኖር ወደ መኖር
ያመጣኸኝ እግዚአብሔር
ከፍጥረታት አከበርከኝ
በአምሳልህ እኔን ፈጠርከኝ
በአርአያህ እኔን ፈጠርከኝ
ለፈጣሪ ለስላሴ
ሳትሰለች ትዘምር ነፍሴ
ስሙን ጠርታ እረክታለች
እንደ መልካም ዛፍ ለምልማለች
የምወጣው የምገባው
ሁሉን ነገር የማደርገው
ጀምሬም የምቋጨው
እግዚአብሔርን ጠርቼ ነው
ሥሉስ ቅዱስ ያከብራሉ
ባለሟልም ያደርጋሉ
በስላሴ ከብሬአለሁ
ልጅነትን አግኝቻለው
← መዝሙር