ምስጋና ለሥላሴ

ከአርያም ይሰማል ከደብረ መቅደሱ
ምስጋና ለሥላሴ ለንጉሱ
ስልጣናት መናብርት ኃይላት መኳንንት
በሰልፍ አጊጠዋል በአማረው ስርዓት
በጉም ጢስ ተሞልቷል የእሳት መድረኮቹ
ዘለዓለም ምስጉን ነው በአገልጋዮቹ
አዝ..................
ዙፋኑን ይዘዋል ኪሩቤል በፍርሀት
ያጥናሉ ሱራፌል መንበሩን በትህጋት
በእሳት መንጦላይዕት ክብሩንም ሰውሯል
በደማቅ ብርሃን እልፍኙን አድምቋል
አዝ....................
ከአርያም በላይ ይልቃል ቁመቱ
ከበርባኖስ በታች ያልፋል መሰረቱ
በስፋት ይርቃል እጅጉን ከአድማሳት
ዓለምን ያያታል በመዳፉ ይዟት
አዝ....................
በዮርዳኖስ ባህር እንዲሁ በታቦር
በዓይናችን አይተናል ተገልጦልን ምስጢር
ክብሩንም ለመውረስ በአምሳሉ ፈጥሮናል
የማይቆም ምስጋና ለስሙ ይዘናል
አዝ...................
ዘማሪ አንዳርጌ አሰፋ፣ ለምለም ከበደ
← መዝሙር