ምስጋናዬ ለአምላኬ አቀርባለሁ
✦
ምስጋናዬ ለአምላኬ አቀርባለሁ
በማደርያው ገብቼ እስግድለታለሁ
ኤልሻዳይ ነው ጌታ ሁሉን ቻይ
ይፈፀማል አምናለሁ የልቤ ጉዳይ፪
አ.ዝ================
ዘንባባዬን ይዤ እንደ ህፃናቱ
ሆሳህና ልበለው ሰግጄ በፌቱ
ምንም ባዶ ብሆን እውቀት ቢጎለኝ
ለስሙ ልዘምር ከልካይም የለኝ፪
አ.ዝ================
አምላኬ በፌትህ ቃል አለብኝ እኔ
ቋንቋዬ መዝሙር ነው ያንተ እንደመሆኔ
በአሚናዳብ ደጃፍ በቅድመ ታቦቱ
ያየክብርህ ሁደት ጠራኝ ማህሌቱ፪
አ.ዝ===============
የህይወት ትርጉሜ አንተ ነህ ደስታዬ
ስምህን ማገልገል ክብሬ ነው ስራዬ
ለታመነው ጌታ ምስክር የሆኑ
ከብረው ተመለሱ ለበረከት ሆኑ፪
አ.ዝ================
መነሻዬ አንተ ነህ ጉልበቴና ክብሬ
መድረሻዬም አንተ መደምደሚያ ቅጥሬ
በፅዮን ተራራ ስትገለጥ ያኔ
ነጩን ልብስ አልብሰህ አስነሳኝ ለቅኔ/፪
በማደርያው ገብቼ እስግድለታለሁ
ኤልሻዳይ ነው ጌታ ሁሉን ቻይ
ይፈፀማል አምናለሁ የልቤ ጉዳይ፪
አ.ዝ================
ዘንባባዬን ይዤ እንደ ህፃናቱ
ሆሳህና ልበለው ሰግጄ በፌቱ
ምንም ባዶ ብሆን እውቀት ቢጎለኝ
ለስሙ ልዘምር ከልካይም የለኝ፪
አ.ዝ================
አምላኬ በፌትህ ቃል አለብኝ እኔ
ቋንቋዬ መዝሙር ነው ያንተ እንደመሆኔ
በአሚናዳብ ደጃፍ በቅድመ ታቦቱ
ያየክብርህ ሁደት ጠራኝ ማህሌቱ፪
አ.ዝ===============
የህይወት ትርጉሜ አንተ ነህ ደስታዬ
ስምህን ማገልገል ክብሬ ነው ስራዬ
ለታመነው ጌታ ምስክር የሆኑ
ከብረው ተመለሱ ለበረከት ሆኑ፪
አ.ዝ================
መነሻዬ አንተ ነህ ጉልበቴና ክብሬ
መድረሻዬም አንተ መደምደሚያ ቅጥሬ
በፅዮን ተራራ ስትገለጥ ያኔ
ነጩን ልብስ አልብሰህ አስነሳኝ ለቅኔ/፪
✦