ምስጋናዬን ላምላኬ አቀርባለው

ምስጋናዬን ላምላኬ አቀርባለው
በማደሪያው ገብቼ ሠግድለታለው
ኤልሻዳይ ነው ጌታ ሁሉን ቻይ
ይፈፀማል አምናለሁ የልቤን ጉዳይ/ 2........
ዘንባባዬን ይዤ እደህፃናቱ
ሆሣና ልበለው ሠግጄ በፈቱ
ምንም ባዶብሆን እውቀት ቢጎድለኝ
ለሥሙ ልዘምር ከልካይም የለኝ//2........
አዝ
አምላኬ በፈትህ ቃል አለብኝ እኔ
ቋንቋዬ መዝሙር ነው ያንተ እደመሆኔ
ባሚናዳ ደጃፍ በቅድመ ታቦቱ
ያየክብርህ ውደር ጠራኝ ማህሌቱ ///2
አዝ
የህይወት ትርጉሜ አንተነህ ደሥታዬ
ስምህን ማገልገል ክብሬነው ሥራዬ
ለታመነው ጌታ ምስክር የሆኑ
ከብረው ተመለሱ ለበረከት ሆኑ///2.......
አዝ
መነሻዬ አንተነህ ጉልበቴና ክብሬ
መድረሻዬም አንተ መደምደሚያ ቅጥሬ
በፂሆን ተራራ ስትገለጥ ያኔ
ነጩን ልብሥ አልብሠህ አስነሳኸኝ ለቅኔ
← መዝሙር