ሞቼ ስለማልቀር
✦
ሞቼ ስለማልቀር ትንሣኤ ስላለኝ
በተስፋ ቤታችን ስለምንገኛኝ
ወዳጅ ዘመዶቼ አታልቅሱ በቃኝ፪
አቀናለሁና ገና አዲስ ኑሮ
አምላክን አስቡት ይብቃችሁ እሮሮ፪
ይልቅ ጸልዮላት ለነፍሴ እረፍት
ዓለም አታላይ ናት ዘላቂ አይደለች
ለሥጋ ነው እንጂ ለነፍስ አትመች፪
ግን ከሥጋ ጋር ስንኖር ትእዛዙን ከጠበቅን
ለተዘጋጀው ቤት ወራሾች እኛው ነን፪
መቼም ከማያልቀው በረከት ያደልከን
ዘላለማዊ ሕይወት ለሰጠኽኝ
ምስጋናችን ይድረስህ ጸጋህ አይለየን
እኛ በድለን ትህዛዝህን ጥሰን
አንተ በመስቀል ላይ ደምህ ፈሰሰልን
ፍቅርህን ስናስብ እጅግ ይደንቀናል
ለዚህ ሁሉ ውለታህ ምን እንከፍላለን
በተስፋ ቤታችን ስለምንገኛኝ
ወዳጅ ዘመዶቼ አታልቅሱ በቃኝ፪
አቀናለሁና ገና አዲስ ኑሮ
አምላክን አስቡት ይብቃችሁ እሮሮ፪
ይልቅ ጸልዮላት ለነፍሴ እረፍት
ዓለም አታላይ ናት ዘላቂ አይደለች
ለሥጋ ነው እንጂ ለነፍስ አትመች፪
ግን ከሥጋ ጋር ስንኖር ትእዛዙን ከጠበቅን
ለተዘጋጀው ቤት ወራሾች እኛው ነን፪
መቼም ከማያልቀው በረከት ያደልከን
ዘላለማዊ ሕይወት ለሰጠኽኝ
ምስጋናችን ይድረስህ ጸጋህ አይለየን
እኛ በድለን ትህዛዝህን ጥሰን
አንተ በመስቀል ላይ ደምህ ፈሰሰልን
ፍቅርህን ስናስብ እጅግ ይደንቀናል
ለዚህ ሁሉ ውለታህ ምን እንከፍላለን
✦