ሞተ ስለእኛ

ሞተ ስለእኛ
የነገሥታት ንጉሥ የኃያላን ዳኛ
ሞተ ስለኛ
ጐለጐታ እስኪደርስ ስቃይ ተቀበለ
ሥጋዉ ተዳከመ በመከራ ዛለ
በጅራፍ ተገርፎ ደም ነጠበ ገላዉ
ሞተ ስለኛ
ሚካኤል ዝም አለ ተገርሞ አስተዋለ
ገብርኤል ሰይፉን ወደ ምድር ጣለ
ከዋክብት ደንግጠዉ ረገፉ ዛሬ
መላእክት አለቀሱ ቀረና ዝማሬ
ሞተ ስለኛ
ዑራኤል አምላኩን በመሰቀል ላይ አየ
በብርሃን ጽዋ ደሙን ተቀበለ
ዕንባዉ አላቆመም ጌታዉ ሲንገላታ
ተገርሞ አስተዋለ በጥፊ ሲመታ
ሞተ ስለኛ
← መዝሙር