ሞተሃልና ስለኔ

ሞተሃልና ስለእኔ ምንም ሳይኖርብህ ጥፋት
ተከሰህ ተወቅሰህ በጲላጦስ ፊት
ኢየሱስ አማለከ ምሕረት ስብሐት ለከ
የአንተ መንገላታት ሁልጊዜ ያሳዝነኛል ሲወራ
በመስቀል ላይ ሆነህ ያየኸው መከራ
ኢየሱስ የህይወት እጀራ ስብሐት ለከ.2/
ከልኡል ቦታ ዝቅ ብለህ ፈጣሪ ፍጡራን አምላክ
በሰው ፊት ተዋርደህ ስለሰው የሞትክ
በመስቀል ላይ ተጠማሁ እያልክ ስብሐት ለከ/2
መሐሪ ጌታ ሆይ አሁንም እንደ ቸርነትህ ብዛት
የእኛን በደል ሁሉ ሳትመለከት
አድነን ከዳግመኛ ሞት ስብሐት ለከ
← መዝሙር