ሞትን ድል አድርጎ

ሞትን ድል አድርጎ ተነስቷል
የትንሳኤው ጌታ አማኑኤልህ
ሞትን ድል አድርጎ ተነስቷል
የሰራዊት ጌታ መዳኒዓለምህ
ትንሳኤውን ልታይ ማርያም መግደላዊት
ሄደች ወደ አምላኳ ተነስታ በለሊት
የለም ከመቃብር ተነስቷል ከሙታን
እሰይ ደስ ይበል አይተናል ብርሃን
ሉቃስ ቀለዩጳ ድካማችሁ ይብቃ
ቆመናል በደስታ ብራሃናችን ደምቃ
ሂዱ ለዓለም አውሩ የእርሱን ድንቅ ስራ
ታላቁን ብርሃን ለዓለም ስያበራ
ብርቱ ነው ጠንካራ መቼም የማይረታ
የሲኦል ሰንሰለት በሐይሉ ተፈታ
ከዘላለም ስቃይ ነፃ ወጥተናል
ከክርስቶስ ጋራ በድል ቆመናል
መላዕክት ነጭ ለብሰው ዜናን አበሰሩ
የጌታን ትንሳኤ ለዓለም ተናገሩ
ተነስቷል ኢየሱስ ከመቃብር የለም
ሲኦል ባዶ ቀረች ለእኛም ሆነ ሠላም
← መዝሙር