ሙሽራ ሙሽራ
✦
ሙሽራው፬ እጹብ ነው ደስታው ሙሽራው
ሙሽራዋ፬ እጹብነው ደስታዋ ሙሽራዋ፪
አዝ ---
እንደ አዳይ አበባ ሙሽሮች ፈክታችሁ
በለመለመ መስክ ያለ ፍሬ መስላችሁ
ልክ እንደ ጨረቃ እንደሰማይ ፀሐይ
መልካሙ ሥራችሁ በራ በአደባባይ
ካባዋን ደርባ በጥበቡ ላይ
የተዋሕዶ ልጅ ደምቃ ስትታይ
በቤተክርስቲያን ሥርዓት በማደጓ
ይኸው መሠከረ የሙሽሪት ሠርጓ
መልካም ስነምግባር ፍቅር የከበበህ
የእመብርሃን ልጅ አቤት ማማርህ
ከመቼውም በላይ ዛሬ ተውበሃል
የአማኑኤል ግርማ ዙሪያህን ከቦሃል
መልካም ሥነምግባር ፍቅር የከበበሽ
የእመብርሃን ልጅ አቤት ማማርሸ
ከመቼውም በላይ ዛሬ ተውበሻል
የአማኑኤል ግርማ ዙሪያሽን ከቦሻል
የእመቤቴ ፀዳል ዙሪያሸን ከቦሻል
ሙሽራዋ፬ እጹብነው ደስታዋ ሙሽራዋ፪
አዝ ---
እንደ አዳይ አበባ ሙሽሮች ፈክታችሁ
በለመለመ መስክ ያለ ፍሬ መስላችሁ
ልክ እንደ ጨረቃ እንደሰማይ ፀሐይ
መልካሙ ሥራችሁ በራ በአደባባይ
ካባዋን ደርባ በጥበቡ ላይ
የተዋሕዶ ልጅ ደምቃ ስትታይ
በቤተክርስቲያን ሥርዓት በማደጓ
ይኸው መሠከረ የሙሽሪት ሠርጓ
መልካም ስነምግባር ፍቅር የከበበህ
የእመብርሃን ልጅ አቤት ማማርህ
ከመቼውም በላይ ዛሬ ተውበሃል
የአማኑኤል ግርማ ዙሪያህን ከቦሃል
መልካም ሥነምግባር ፍቅር የከበበሽ
የእመብርሃን ልጅ አቤት ማማርሸ
ከመቼውም በላይ ዛሬ ተውበሻል
የአማኑኤል ግርማ ዙሪያሽን ከቦሻል
የእመቤቴ ፀዳል ዙሪያሸን ከቦሻል
✦