ሙሽራው ከሙሽሪት ጋር

ሙሸራው ከሙሽሪት ጋር
በአደባባይ ደምቀው ታይተዋል
እልል በሉ ሚዜዎቹ /ሚዜዎቿ/
የደስታ ተካፋዩቹ/ተካፋዩቿ/
እስቲ ዘምሩለት ለሙሽራው
በአንድነት ሆናችሁ
ወደ አዲሱ ቤት ለሙሽራው
መግባቱን አይታችሁ
እስቲ ዘምሩላት ለሙሽሪት
በአንድነት ሆናችሁ
ረዳት አገኘች የእኛ ሙሽራ
ጥሩ ወንድምን
አዝ ---
ሥነምግባር ላለው ለሙሸራው
የቀና ሃይማኖት
ደስታው ደስታችን ነው የሙሸራው
ክብሩም ክብራችን ነው
ሥነምግባር ላላት ለሙሽሪት
የቀና ሃይማኖት
አጅቧት በደስታ ሙሽሪትን
በሆታ በእልልታ
አዝ ---
ስትበቁ ለክብር ለሙሽሮቹ
ለመልካም ትዳር
ጎጆ ስትቀልሱ ለሙሽሮቹ
በእግዚአብሔር ፈቃድ
አብነት ለመሆን የእኛ ሙሽሮች
ለጓደኞቻችሁ
ወልዳችሁ ለመክበድ የእኛ ሙሽሮች
እግዚአብሔር ይርዳችሁ
← መዝሙር