ሙሽራዬ
✦
ሙሽራዬ ፬
በእግዚአብሔር ፈቃድ አንድ ሆነዋል ዛሬ
በእመብርሃን ፈቃድ አንድ ሆነዋል ዛሬ
በእግዚአብሔር ፈቃድ አንድ ሆነዋል ዛሬ
በእመብርሃን ፈቃድ አንድ ሆነዋል ዛሬ
የተሰጣቸውን መክሊት ሳይሸሽጉ
በበረከት ፍሬ በቅተዋል ለሠርጉ
በቃሉ ተቃኝታ ተውባ ነፍሳቸው
አምረዋል ሙሽሮች ተክሊል ተቀዳጅተው
በበረከት ፍሬ በቅተዋል ለሠርጉ
በቃሉ ተቃኝታ ተውባ ነፍሳቸው
አምረዋል ሙሽሮች ተክሊል ተቀዳጅተው
ሙሽራዬ ፬
በእግዚአብሔር ፈቃድ አንድ ሆነዋል ዛሬ
በእመብርሃን ፈቃድ አንድ ሆነዋል ዛሬ
በእግዚአብሔር ፈቃድ አንድ ሆነዋል ዛሬ
በእመብርሃን ፈቃድ አንድ ሆነዋል ዛሬ
ከሀገረ ሰላም ወጥተው ከመቅደሱ
በረከትን አፍሰው በክብር ተነሡ
በወንጌል ታሽተዋል ጣፍጠዋል በቃሉ
ሆነዋል ሙሽሮች የእግዚአብሔር አካሉ
በረከትን አፍሰው በክብር ተነሡ
በወንጌል ታሽተዋል ጣፍጠዋል በቃሉ
ሆነዋል ሙሽሮች የእግዚአብሔር አካሉ
ሙሽራዬ ፬
በእግዚአብሔር ፈቃድ አንድ ሆነዋል ዛሬ
በእመብርሃን ፈቃድ አንድ ሆነዋል ዛሬ
በእግዚአብሔር ፈቃድ አንድ ሆነዋል ዛሬ
በእመብርሃን ፈቃድ አንድ ሆነዋል ዛሬ
በደም ተገንብቷል የቤታቸው መቃን
ታጥረዋል በፍቅሩ በማይፈርሰው ኪዳን
ወደመንደራቸው አቀና ንጉሡ
ጠርተውታልና በሠርጉ ሳይረሱ
ታጥረዋል በፍቅሩ በማይፈርሰው ኪዳን
ወደመንደራቸው አቀና ንጉሡ
ጠርተውታልና በሠርጉ ሳይረሱ
ሙሽራዬ ፬
በእግዚአብሔር ፈቃድ አንድ ሆነዋል ዛሬ
በእመብርሃን ፈቃድ አንድ ሆነዋል ዛሬ
በእግዚአብሔር ፈቃድ አንድ ሆነዋል ዛሬ
በእመብርሃን ፈቃድ አንድ ሆነዋል ዛሬ
✦