ሙሽራዮ

ሙሽራዬ አበባዬ
ከጐንህ የምትሆን እህት አገኘህ
የኛማ ሙሸራ እንኳን ደስ አለህ
የእግዚአብሔር ፈቃዱ ለዚህ ካበቃችሁ
ቤታችሁ ይመረቅ በፍቅር ያጽናችሁ
አዝ ---
ወንድም አግተሻል የሚያስብልሽ
የእኛማ ሙሽራ እንኳን ደስ አለሽ
እግዚአብሔር ይመስገን እኛም ደስ ብሎናል
በቤተክርስቲያን ሠርጋችሁ ውብ ሆኖአል
አዝ ---
እንደነፍስህ አርገህ እንድትወዳት
አደራ ሰጠንህ በጌታችን ፊት
እንድታስቢለት አንቺም ለአካልሽ
አደራ ትላለች ወንጌል እናትሽ
አዝ ---
በሥጋው ወደሙ ሕይወት አግኝታችሁ
ፍሬአችሁም ይብዛ ይባረክ ጓዳችሁ
አምላክ ያለበት ነው ይሄ ጋብቻችሁ
እስከ መጨረሻው ኑሩ ደስ ብሎአችሁ
አዝ ---
← መዝሙር