ሙሽሮች እንኳን ደስ አላችሁ

ሙሽሮች እንኳን ደስ አላችሁ
ለዚህ ቀን ይኸው ደረሳችሁ
በአምላክ ፊት እጅግ ከበራችሁ
በእግዚአብሔር ቸርነት በመልካም ፈቃዱ
በቅዱስ ቁርባኑ ዛሬ ተዋሐዱ
በሥርዓተ ተክሊል በሥጋ ወደሙ
በመድኃኔዓለም ፊት ጋብቻን ፈጸሙ
አዝ ---
በቤተክርስቲያን በፈጣሪያቸው ፊት
ሁለቱም አንድ ሆኑ በዚህች ቅድስት እለት
አንድ የሚያደርጋቸው ተነቦ ወንጌሉ
በካህኑ መስቀል በረከት ታደሉ
አዝ ---
በወንጌል ትእዛዝ በሐዋርያት ቃል
በእመብርሃን ፊት ጋብቻቸው ሰምሮአል
በአምላክ ሥጋና ደም ሁለቱም ታተሙ
የኅብረት ቃልኪዳን በአንድ ላይ አሰሙ
አዝ ---
ጸንቶ የሚያዘልቃቸው የማይለያያቸው
ክቡር ቃል ስላለ በመካከላቸው
እስከመጨረሻው አንድ አካል ሆነዋል
የአማኑኤል ሥጋ አስተሳስሮአቸዋል
አዝ ---
← መዝሙር