ሙታንን ያድን ዘንድ

ሙታንን ያድን ዘንድ የሞት ሞትን ሽሮ
ወልደ አምላክ ሄደ ወደ ኋላ ታሥሮ
ምን በበደለ ነው ምን ባደረገ ነው
ወልድ እንደ ቀማኛ ሲገረፍ የዋለው
ቅዱሳን እጆቹ አዳምን የሠሩት
ቅዱሳን እግሮቹ በገነት የዙሩት
ተቸንክረው ዋሉ በጠንካረው ብረት
ግርማን ለኪሩቤል ያጎናጸፋቸው
ዘውድን ለሱራፌል የሚያቀዳጃቸው
ከለሜዳ ለብሶ ዋለ ከፊታቸው
ሔዋን በፈጸመችው የበደልን ሥራ
አዳም በፈጸመች የበደልን ሥራ
ቸሩ ወልደ አምላክ ዋለ በመከራ
ጌታ በፈቃዱ አጁን ቢሰጣቸው
ተዘባበቱበት የሾህ አክሊል ደፍተው
ትንሹም ትልቁም ሲዘባቱብህ
ዋ ምን ይደንቃል ታላቁ ትዕግስትህ
ዘማሪ ታዕካ ነገሥት በዓታ ሰንበት ት/ቤት
← መዝሙር