ና ና የምስጋና

ናና የምስጋና ጌታ ናና የምሕረት ጌታ
ማዳንህ ተገኝታለችና ሰላምህ ተገኝታለችና
ኢየሩሳሌም ሆይ ምስጋና ጀምሪ
መለከትን ንፊ ነጋሪት ጎስሚ
ሰላምሽ ታውጇል መዳንሽም ቀርቧል
ጌታ ሊጎበኝሽ ከበራፍሽ ቆሟል
አዝ………………………………….
ያልታደልሽው ሀገር ጌርጌስዮን ሆይ
ለምን ተቃወምሽው አምላክሽን ስታዪው
የከተማውን በር መዝጊያውን ቆልፈሽ
ከሩቅ የሸኘሽው ሲመጣ ሰላምሽ
አዝ………………………………..
የቢታንያ ድንጋይ አንደበት አውጣቶ
ምስጋና ጀመረ አምላኩን ለይቶ
ሣርና ቅጠሉ ዘንባባው ሰገደ
ፍጥረት ሊያመሰግን አምላኩን ወደደ
አዝ…………………………………
ሕፃን ሽማግሌው ምስጋና ሲያቀርቡ
ተቆልፎ ነበር ፈሪሳዊ ልቡ
ዛሬም ለምስጋና ልባችን ይለወጥ
ሆሳዕና ጌታ ይመላለስበት
← መዝሙር