ነዓ በልዑል

ነዓ በልዑል
የጌታ ባለሟል ቅዱስ ሚካኤል
ሰይጣን ስልጣን ሲሻ አምላክን ለመሆን
ተለየ ከክብሩ ወርዶ ከሥልጣን
በታማኝነት ህ ጸንተህ በመቆምህ
በመላእክት ላይ ልዑል አደረገህ
ነዓ በልዑል
የጌታ ባለሟል ቅዱስ ሚካኤል
እስራኤላውያን በሙሴ ሲመሩ
ጽኑ አደረካቸው ክፉን እንዳይፈሩ
በአንተ ረዳትነት ተከፍሎ ባሕሩ
እነርሱም በአንድነት ሄዱ ተሻገሩ
ነዓ በልዑል
የጌታ ባለሟል ቅዱስ ሚካኤል
ባሕራን የዋሁ ሰው የሞት ጥሪ ይዞ
ወደ አጥፊዎች ሀገር እያለ በጉዞ
በሰው ተመስለህ ፈጥነህ ደርሰህለት
የሞቱን ድብዳቤ በሕይወት ለወጥክለት
ነዓ በልዑል
የጌታ ባለሟል ቅዱስ ሚካኤል
የአፎም ያ አባት አጽናኝ አለኝታዋ
ረዳቷ ነበረ ምስልህ ጠባቂዋ
በአንተ ተመስሎ ሰይጣን ሲፈትናት
በሚያስፈራው ግርማህ ፈጥነህ ደረስክላት
ነዓ በልዑል
የጌታ ባለሟል ቅዱስ ሚካኤል
← መዝሙር