ነቢይ እንዲህ ብሎ የተነበየልሽ

ነቢይ እንዲህ ብሎ
ነቢይ እንዲህ ብሎ የተነበየልሽ
ኃይልሽን ልበሺ ወገብሽን ታጥቀሽ
ወላዲተ አምላክ ድንግል አንቺ እኮ ነሽ
ነውርና ነቀፋ ፍጹም የሌለብሽ
የምድር ነገሥታት ላንቺ ይሰግዳሉ
የእግርሽንም ትብያ ወድቀው ይልሳሉ
ፈጣሪ ድንግልን ሲፈጥራት ጀምሮ
እንዳልተዳደፈች ጠንቅቆ መርምሮ
ሊቁ ቴዎዶቶስ በድርሳኑ ጽፏል
አባ ጊዮርጊስም እርሱን ተከትሏል
ከጽንሷ ጀምሮ ከእናቷ ማኅፀን
መች ሌላ ነበረ የጠበቃት እርሷን
ጰራቅሊጦስ እንጂ ሁሉን የሚያነብብ
ማሕያዊ ጌታ የሠረፀ ከአብ
ብሎ ጽፎልናል በድርሳነ ዐርጋኖን
እንድንጸልየው ምዕመናን ሁላችን
← መዝሙር