ነፍሴ ሆይ
✦
ነፍሴ ሆይ እግዚአብሔርን በቅን አገልግይ፪
የተቀበለው በቀራንዮ
ያን ሁሉ መከራ በመስቀሉ ላይ
ለአንቺ ሲል ነውና ነፍሴ ሆይ
ተዘጋጅተሸ ኑሪ ሁልጊዜ
በነገ በዛሬ እንዳትታለዪ፪ ነፍሴ ሆይ
በንስሓ ጥምቀት ታጠቢና
ክቡር ደሙን ጠጪ ሥጋውንም ብይ፪
ነፍሴ ሆይ
ዘላለም በደስታ እንድትኖሪ
ከዘላለም ቤትሽ መንግሥተ ሰማይ፪
ነፍሴ ሆይ
የተቀበለው በቀራንዮ
ያን ሁሉ መከራ በመስቀሉ ላይ
ለአንቺ ሲል ነውና ነፍሴ ሆይ
ተዘጋጅተሸ ኑሪ ሁልጊዜ
በነገ በዛሬ እንዳትታለዪ፪ ነፍሴ ሆይ
በንስሓ ጥምቀት ታጠቢና
ክቡር ደሙን ጠጪ ሥጋውንም ብይ፪
ነፍሴ ሆይ
ዘላለም በደስታ እንድትኖሪ
ከዘላለም ቤትሽ መንግሥተ ሰማይ፪
ነፍሴ ሆይ
✦