ነፍሴን አደራ

እይራየኒ አይነሙት
ወይርከበኒ ኩነኔ
ነፍሴን አደራ በሰማይ ተክልዬ ፀሃይ
ፅላሌ ዞረሪ ነይ መስክሪ
የተክለሃይማኖትን ዝና አውሪ
የእንቁርቁሪት ጸበል ማር ወተት
ሁሉም ተፈወሱ ሲጠጡት
ትህትናህ ግሩም ነው ቅድስናህ
ሀይቅ እስጢፋኖስ አገልግለህ
ደብረ ዳሞ ዘልቀህ ክንፍ አወጣህ
ደብረ ሊባኖስ ላይ አርፏል አፅምህ
ፈተታና ዳሞት ተሻግረህ
ባርያንን ሁሉ አሳፈርክ
በንብ ቀፎ አርገው ቢጥሉህ
ሚካኤል በክንፉ አቀፈህ
በደብረ አሰቦት ጦር ተክለህ
29 ዘመን ተጋድለህ
ወዝህ ያረፈበት ነጠብጣቡ
ድውይ ይፈውሳል ቃል ኪዳኑ
ይህን ሁሉ ጸጋ ተችረሃል
ቁጥርህ ከመላዕክት ተስተካክሏል
አባቴ እኔ ስልህ
ነፍሴን ታደግልኝ በምልጃህ
← መዝሙር